ግልጽ የጨረታ ማሰታወቂያ

0
41

በደብረ ማርቆስ ከተማ አብማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት አመት ለሥራ አገልግሎት የሚዉሉ 1ኛ ዙር በሎት ጠቅላላ ድምር ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ እና ሎት 3 ኮምፒውተርና ተዛማጅ  ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች  መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የሚገዙትን ዕቃ አይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸዉን፣ ፊርማቸንና ሙሉ አድራሻቸዉን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች ሳምፕል ላልቀረበባቸዉ የግዥ ሎት በተጠየቀዉ ዝርዝር መሰረት ያሸነፈዉ ድርጅት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ያቀረቡት ሳምፕል ዉል ይዘዉ ዕቃዉ ገቢ ከተደረገላቸዉ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል አብማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 የመጫረቻ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በሚሞሉት ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአብማ ክፍለ ከተማ ስም በተዘጋጀ መሂ-1 ደረሰኝ 2 በመቶ በመቁረጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ወይም ለግዥ ኦፊሰሮች ዘወትር በስራ ሰዓት መስጠት የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ይቆያል፡፡
  12. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት አብማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው /የውክልና ማስረጃ በመያዝና ፎቶ ኮፒውን በማስረከብ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ የጨረታ መክፈቻዉ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. አሸናፊዉ ድርጅት አብማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለበጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 058 178 37 93 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አብማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here