የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተሮች አገልግሎት የሚዉሉ የጽህፈት መሳሪያዎችን ማለትም፡-
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት | ዝርዝር መግለጫ |
| 1 | ወረቀት የኮፒውተር | በደስታ | 300 | ጥርት ብሎ የሚወርድ ኬኒያ ቢክ 1ኛ ደረጃ |
| 2 | ቢክ እስክርቢቶ ሰማያዊ | በፓኮ | 183 | ጥርት ብሎ የሚወርድ |
| 3 | መዝገብ መካከለኛ | በቁጥር | 65 | 150 እና ከዚያ በላይቅጠል ያለው 25×35 /የውጭ/ |
| 4 | ፕሮቶኮል መዝገብ | በቁጥር | 23 | |
| 5 | ጥቁር እስክርቢቶ ቢክ | በፓኮ | 18 | ጥርት ብሎ የሚወርድ |
| 6 | ማስታወሻ ደብተር | በቁጥር | 145 | ባለ 100 ቅጠል ዋተር ፕሩፍ |
| 7 | የእጅ ካርቦን | በደስታ | 35 | 8000 |
| 8 | አቃፊ | በቁጥር | 75 | የብረት |
| 9 | ክላሰር | በደስታ | 1000 | ወፍራም |
| 10 | አቃፊ | በቁጥር | 195 | ባለ ገመድ |
| 11 | ላስትሮ | በቁጥር | 25 | ትልቁ በደንብ የሚይዝ |
| 12 | ትልቁ እስቴፕረር መምቻ | በቁጥር | 2 | 23 s 17 kangaroo |
| 13 | ፖስታ | በደስታ | 20 | ትንሹ |
| 14 | ባለ መስመር ወረቀት | በደስታ | 09 | |
| 15 | የእስቴፕለር ሽቦ | በፓኮ | 65 | ትንሹ |
| 16 | የእስቴፕለር ሽቦ | በፓኮ | 02 | ትልቁ |
| 17 | ፕሪተር ቀለም | በትዩብ | 78 | 26A |
| 18 | ፖስታ | በደስታ | 16 | መካከለኛ |
| 19 | ኮሬክሽን ፍሉድ | በቁጥር | 45 | ባለ ጠጠር |
| 20 | ፖስታ | በደስታ | 09 | ትልቁ |
| 21 | ካልኩሌቴር | በቁጥር | 10 | ባለ 3 ዜሮ |
| 22 | የዘመኑ አጀንዳ | በቁጥር | 10 | የውጭ |
| 23 | የኮፒ ማሽን ቀለም | በትዩብ | 12 | C xv 42 canon |
| 24 | ማህተም ቀለም | በትዩብ | 25 | |
| 25 | ስታምፕ ፓድ | በቁጥር | 07 | |
| 26 | የወረቀት መብሻ መካከለኛ | በቁጥር | 05 | ካንጋሮ መካከለኛ |
| 27 | የስቴፕረር መምቻ | በቁጥር | 12 | ትንሹ |
ስለሆነም በዝርዝሩ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በስራ ዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በማሸግ አየሁኝ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 የጨረታ ፓስታዉን አሽገዉ ስምና አድራሻ በመፃፍ በጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ወይም ለግዥ ኦፊሰር ወይም ለቡድን መሪ ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በስራ ሰዓት ሠነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በ3፡30 ይዘጋና በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- የዋጋ መሙያ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ የሌለዉ መሆን ይኖርበታል፡፡ ቢኖር ግን ፊርማ መኖር አለበት፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ ድርጅት የሚለየዉ በሎት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ እቃ /አግልግሎት/ እስከ አየ/ጓ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አየሁ/ጓ/ወ/ገ/ኢ/ት/ግዥና ንብረትአስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 327 80 95 /09 18 78 03 22 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

