ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለመ/ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ሎት 1፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 2፣ የተለያዬ ህትመቶች ሎት 3፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች ሎት 4 እና የጽዳት እቃዎች ሎት 5 በግልጽ ጨረታ የግዥ አወዳድሮ መግዛት እና በህትመት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ይህ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ በደ/ታቦር ከ/ወ/ፍ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ በመምጣት ከዋናዉ ጋር ሊገናዘብ የሚችልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ ለእያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ (ሲፒኦ) ወይም የጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገዉ ደ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ብለዉ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ እስከ 16ኛዉ ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን የሚታሸገዉም በዚሁ ሰዓት ነዉ፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባገኙም በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡45 ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊዉ የሚሆነዉ በጥቅል /በሎት/ ነዉ፡፡ ነገር ግን ከቀረቡት እቃዎች አንድም እቃ ያልሞላ ከዉድድር ወጭ ነዉ፡፡
  10. የሚገዙ እቃዎች ርክክቡ የሚፈፀመዉ በሙያተኛ ተረጋግጦ ነዉ፡፡
  11. አቅርቦት ደጎ/ዞን/ደ/ታቦር ከ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ይሆናል፡፡
  12. የሚገዙት እቃዎች (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 141 71 78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  15. ተቋሙ ግዥን ከቀረበዉ የዋጋ መጠን 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. አሸናፊዉ የአሸነፋቸዉን እቃዎች በራሱ ወጭ በመጓጓዝ ደ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
  17. ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ማቅረብ አይችሉም፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here