ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

በስሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የጠለምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳዉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች መደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3. የግንባታ ማቴሪያል፣ ሎት 4 የጽዳት እቃ እና ሎት 5 የመኪና ጎማ አገልግሎት የሚውሉ በ2018 ዓ.ም በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ የእቃ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-

  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያላቸው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም በመ/ቤቱ ዋና ገ/ያዥ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ እና (ሲፒኦ) ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ለግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
  4. በማንኛዉም ግዥ ለእቃዎች ብር 20,000 / ሃያ ሽህ ብር/ በላይ እና የአገልግሎት ከግዥ ከብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት እራሳቸዉ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ |ፈቃዳቸዉን በማሳየት ብር 50 /ሀምሳ ሃምሳ ብር/ በመክፈል በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 1 ዘዉትር በስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይበት ቀን ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ /ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በጠለምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ /ን/ አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 1 ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 3 የግንባታ ማተሪያል፣ የጽዳት እቃ እና የመኪና ጎማ ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን የሚያቀርበው እቃ በባለሙያ እየተረጋገጠ በጠለምት ወረዳ ግዥ/ን/አስ/ ቡድን ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ እንዲሁም የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ለቀጣይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
  12. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. ጨረታዉን ለማዛባት የሚሞክር ማንኛዉም ተጫራች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 ዓ.ም እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይደረጋሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዉርስ ይሆናል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ ይህንን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታዉ ዉጤት ቅሬታ ካለ የጨረታዉ ዉጤት በማስታወቂያ ቦርድ ከተገፀበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅሬታቸዉን ለጠለምት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  15. ስለጨረታ ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 28 97 /09 18 73 21 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጠለምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here