ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
71

በምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የቡሬ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቡሬ ከተ/አስ/ሴክተር መ/ቤቶች እና ለCIP ፕሮግራም አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ የጽህፈት መሳያዎች ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋውን በእያንዳንዱ ሎት 1 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ከተ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሬ ከተ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ4፡00 ታሽጎ በ4፡15 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ሲሆን በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ እና እቃዎችን በቡሬ ከተማ አስተዳደር ንብረት ክፍል ድረስ የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
  11. ሁሉም እቃዎች በዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ እና በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም መሆኑ አቅራቢው ሙሉ እምነት ያለው  መሆን አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 11 00 /111 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቡሬ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here