በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደብረ ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የመገናኛ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ. ስኳር ማጓጓዝ በየዙሩ 1101 ኩ/ል ከመተሃራ ወደ ደብረ ታቦር እና ወረታ ከተማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ቢያንስ 200 ኩ/ል እና በላይ መጫን የሚችል መኪና ያላቸዉ እና የመኪናዉን የሊብሮ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ጨረታ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ ከተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት አይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል (በመግዛት) የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ስኳሩን እንዲያጓጉዙ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የተመደበዉን ስኳር ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊዉ በተለየ በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ7 ተኛው ቀን 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 7 ተኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ወጭውን በመሸፈን በደ/ታቦር እና ወረታ ከተማ ከሚገኘው መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ መጋዘን ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
  11. ከላይ የተጠቀሰዉ የስኳር መጠን በተመለከተ የንግድና ገበያ ልማት ተቋም በሚያሳዉቀዉ መሰረት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. የመጫረቻ ዋጋዉ ዉል ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ወራት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  13. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 /058 414 18 05 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመገናኛ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here