ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
50

የመገናኛ ሁለገብ/የገበ/ኅ/ስራ ማህበራት ዬኒየን ኃ.የተወሰነ ከቀድሞው የዩኒየኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ በቁም የሚገኘውን ሁሉንም የጽድና ሌሎች የዛፍ ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ቆርጦ ለሚያነሳ ድርጅት ወይም ግለሰብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ  ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 2 በመቶ በባንክ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራነቲ (ዋስትና ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከዬኒየኑ ቀርቦ የገቢ ደረሰኝ አስቆርጦ ማስያዝ አለበት፤ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መረጃ (በሲፒኦ) ከሆነ ዋናውን፤ ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ ያስያዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ጨረታ ከብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ ከተሰጣቸው አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና ሲፒኦ ሲያሲዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከዬኒየኑ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ስማቸውን፣ የሚወዳደሩበትን ዋጋ፣ ሙሉ አድራሻና ፊርማቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ ማህተማቸውን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥ ሲሆን በ10ኛው ቀን መጨረሻ  8፡30 የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡45 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም  ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዩኒየኑ ቀርቦ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ አስይዞ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን  ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በራሱ ወጭ ዛፉን አስቆርጦና አጓጉዞ እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም  ድረስ  አጠቃሎ ማንሳት አለበት፡፡
  8. አሸናፊው እንጨቱን በሚቆርጥበትና በሚያነሳበት ጊዜ በአካባቢው በሚገኝ የመብራት መስመር፣ የስልክና ውሃ መስመር፣ በቤትና አጥር ላይ፣ በሰውና በእንስሳት ላይ፣ በመሳሰሉት ንብረቶች በስራ ላይ ችግር ቢያጋጥም ወይም ጉዳት ቢደርስ አሸናፊው ተወዳዳሪ ኃላፊነቱን ይወስዳል ወይም ተጠያቂ ይሆናል፡፡
  9. ዪኒየኑ ያወጣውን ግልጽ ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  10. ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ወይም ግማሽ ቀን የዩኒየኑ የስራ ቀን ነው፡፡
  11. ተወዳዳሪዎች የዛፉን ሁኔታ ለማየት ከፈለጉ ከዩኒየኑ ቀድሞ ጽ/ቤት ድረስ ሂዶ ማየት ይችላሉ፡፡
  12. ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 እና 058 141 99 27 /058 141 70 12 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ ፡- ደ/ታቦር ከተማ ጸደይ ዋናው ባንክ አንደኛ ፎቅ

መገናኛ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here