ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ለሚያስገነበው G+4 የቢሮ ግንባታ በመደበኛ በጀት የጥናት እና ዲዛይን እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ዝግጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች

  1. ከላይ በተጠቀሱት የስራ ዘርፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎቸ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የሚሰራው የጥናት እና ዲዛይን እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ዝግጅቱን የያዘ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ 31ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገ/ያዥ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ለስራው የሚያስፈልገው የማማከር ብቃት የመሀንዲሶች አማካሪ ደረጃ 3 እና በላይ ወይም የመሀንዲሶች እና አርኪቴክቶች አማካሪ ደረጃ 3 እና በላይ ሆኖ በአማራ ክልል ከተሞች እና መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም በፌደራል ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ቁጥጥር ባለስልጣን የተረጋገጠ የእድሳት ዘመኑ ያላለፈ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ብር 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች የአሸነፈውን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  10. የጫረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ እና በቴክኒክ ከፍተኛ ነጥብ የሰጠ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም አይተሞች ዋጋ መሞላት ይኖርበታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ 2 ፖስታ ማለትም የቴክኒክና የፋይናሻልን የያዘ ፖስታ በደ/ጥላ/ግ/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት በ31ኛው ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታ ዉድቅ እንደሚያደርግ አዉቀዉ በጥንቃቄ እንዲሞሉ ይደረግ፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here