የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

የጨረታ ቁጥር አብክመ/የሲ/ቤ/ም/አገ/ብግጨ/02/2018

የአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለቢሮ መገልገያ የሚሆን የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪ ፣የኤሌክትሮኒክስ እና የጃንቦ ኬንት ግዥ  በግልፅ ጨረታ  አወዳድሮ  በሎት መግዛት ይፈልጋል፡ ስለሆነም ተጠሪ መ/ቤቱ  የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ደጋፊ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ምዝገባ አስተዳድር በግዥ ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  10. መስ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 1063 ፋክስ 058 320 1183 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here