ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለዘር የማይዉል ሰብሎችና የተለያዩ ብጣሪዎችን ለመሸጥ የዘር ታግ ለማሳተም፣ ጥራቱን ጠብቆ ሊያጭድና ሊወቃ የሚችል የኮምባይን ሀርቨስተር ለመከራየት እና ከየወረዳዎች የተመረተዉን ዘር በአራቱም ጣቢያዎች ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመከራየት በተጨማሪም የፅህፈት፣የፅዳት፣የኤሌክትሮኒክስ እና የኬሚካል ተዛማጅ እቃዎ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ  የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (ቲን) ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው  በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት  ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የትራንስፖርት ተጫራቾች በአንድ ጊዜ ባሏቸው መኪኖች ከ1,600 ኩ/ል በላይ መጫን የሚችሉ መኪኖች በስማቸው የተመዘገበ ሊብሬ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት (ባሕር ዳር) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፣ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን  የበዓላት ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
  7. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  8. የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
  9. ግዠዉን በተመለከተ ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 22 66 002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 09 18 01 69 35 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here