ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች እንዲሁም ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች  ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሞሉ ሁሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የ2018 የበጀት አመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚሞሉትን የእቃን ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት በጥሬ ገንዘብ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን ዋና በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ የሚውል ሲሆን  የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡30-4፡00 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች በሰነዱ የተዘረዘሩት አቃዎችን በሙሉ የመሙላት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ የአንድንም የእቃ ዋጋ ዝርዝር አለሞሙላት ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር (በሎት) ይሆናል፡፡
  9. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ እቃ መሰረዝ መደለዝ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  10. ተጫራቾች የአሸነፍቸውን እቃዎች መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  11. አቅርቦቶች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. አሸናፊው በተጠየቀው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ጥራቱ ተጠብቆ ካላቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  15. መ/ቤቱ በዝርዝሩ የተጠቀሱትን እቃዎች ብዛት 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here