ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የአማራ ክልል ስቴት ዩንቨርሲቲ ለስልጠና አገልግሎት የሚጠቀምበት የምግብ ማብሰያ ኪችን ቤት ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡- ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በዩንቨርስቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 08/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዩንቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ሰነድ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዩንቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከህዳር 08/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2018 ዓ.ም  8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ ህዳር 28/2018 ዓ.ም 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩንቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. ዩንቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ስቴት ዩንቨርሲቲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here