ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
76

የአምባሰል ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ:- ሎት 1 የጽህፈት መሳርያዎች፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ አልባሳት፣ ሎት 3 ጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 5 ቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች እንዲሁም ሎት 6 ፕላንትና ማሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ፡-

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑ ግብር የከፈላችሁ እና ቲን ያላችሁ፡፡
  2. በእያንዳንዱ የሎት ምድብ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ለሆኑ ማንኛውም ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደረበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በማስላት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የክልል የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
  6. የጨረታው ውድድር በየሎቱ ስለሆነ በሚወዳደሩበት የሎት ምድብ ዘርፍ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ በሙሉ መሞላት አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከመጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ 4:45 ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኙት ወይም በስልክ ቁጥር 09 21 51 89 44 /033 224 03 74 በመደወል መጠየቅ ይችላኩ፡፡

የአምባሰል ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here