በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰሜን አቸፈር ወረዳ የሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እና ሎት 5 ቀለም ቀቢ ባለሙያ በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ማሰዳደር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር በፖስታ አሽገዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ማለትም ከህዳር 08/2018 እስከ ህዳር 28/2018 ዓ.ም ድረስ ተሸጦ በህዳር 29/2018 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ በዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን በሊበን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 09 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ወይም የዋጋ መሙያ ቅፅ ከሊ/መ/ደ/ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 09 ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የሚሞሉት ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ወይም የማይነብብ መሆን የለበትም፡፡ ሆኖም ግን ሥረዝ ካለዉ ፊት ለፊት ፓራፍ ወይም መፈረም ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ዉጭ ይደረጋሉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ በሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስተዳደር ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚለየዉ በተሞላ ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃጸም በመመሪያዉ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደርበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝና ኦርጅናል ማስረጃ በማስገባት ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር በፖስታ አሽገዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 27 82 94 29 /09 18 18 63 75 /09 25 33 27 91 ደዉለዉ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

