በደቡብ ወሎ ዞን የወይን አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በመቀናጆ በጀት የውስጥ ለዉስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማሽኖች እስከ ዝርዝር መግለጫቸዉ ያሟሉና የተገለጹ ዝርዝር መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የማሽኖቹ አይነት 1ኛ. ዳምፕ ትራክ፣ 2ኛ. ሎደር፣ 3ኛ. ሞተር ግሬደር፣ 4ኛ. ቫይብሬተር /ሮለር/፣ 5ኛ. የውሃ ቦቲ እንዲሁም 6ኛ. ዶዘር እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ማሽኖች ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረቱ ምርት ማቅረብ የሚችል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር( ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የማሽን የቴክኒክ ብልሽት፣ የስፔር ፓርት ለውጥ እንዲሁም ዘይት ነክ ነገሮች እና የነዳጅ ወጭ ተጫራቹ በራሱ የሚችል፡፡
- የማሽን ኪራይ ስዓት የሚይዘው ለስራው ስራ ስዓት ብቻ ነው፡፡ የተፈጥሮ አደጋዎች ዝናብ እና ተያያዥ ችግሮች ከተከሰቱ የሚያባክነው ስዓት አይያዝም፡፡
- የማሽን መጓጓዣና እና መጫን ማውረጃ እንድሁም ከሚሰራበት ቦታ (ሳይት) ወደ ሌላ ሳይት መጓጓዣ መጫን ማውረጃ ተጫራቾች የሚችሉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሹፌርና የኦፐሬተር እንዲሁም የረዳት አበል እና ሌሎች ወጭዎች ተጫራቹ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃው አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ተዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ 1 ማስያዝ ያለባቸው እና የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተፃፈለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ መግባት ያለበት ሲሆን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል ፓስታ በጥንቃቄ በማሸግ በወይን አምባ ከተማ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ22 ተኛው ቀን 3፡30 ላይ ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የሚሰሩ ስራዎች ላይ 20 በመቶ ብዛት የመጨመር ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ግዥ በጥቅል የሚፈጸም መሆኑን አውቆ ለእንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ ጠቅላላ ለእያንዳንዳቸው ዋጋ ያለመሙላት ከጨረታው ውድቅ ያስደርጋል፡፡ እንድሁም አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ስራዎች ሙሉ በሙሉ ሰርተው ካላስረከቡ ክፍያ የማይፈፀም ይሆናል፡፡
- ለስራው የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሰርቪስ አገልግሎቶችን አሸናፊው ተጫራች የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- መንገዱ በደቡብ ወሎ ዞን በለገሂዳ ወረዳ በሆነችው በወ/አምባ ከተማ ውስጥ የሚሰራ ሲሆን ገረጋንቲ የሚመረትበት ቦታ ወይም ኳሪ ሳይት ከ4 እስከ 6 ኪሎ ሜትር ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 05 04 46 07 /09 14 35 70 00 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የወይን አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት

