ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

በወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና ተ/ጽ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት ግዥ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች እንዲሁም ሎት 4 የመኪና ዘይትና ቅባት በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟማላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑና የምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም እቃ በኦርጅናል መሙላትና እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም አላቂ የጽህፈት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያዩ ቀለሞችን እና ሌሎች በባለሙያ የሚፈተሹ እቃዎችን በራሳቸው ወጪ በባለሙያ ማስፈተሸ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ስምና ፊርማ፣ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገጹ ማህተም ማድረግ እና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን እንዲሁም (ቫት) ዊዝሆልድን 7.5 በመቶ ታሳቢ ተደርጎ መሞላት አለበት፡፡
  7. ውድድሩ በድምር ዋጋ (ሎት) መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታ ሰነዶችን ለያንዳንዳቸው ሎቶች ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ወጥቶ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜው እሁድ ቅዳሜ ወይም የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የሚከፈት ይሆናል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን (የመቀበል) ግዴታ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/፣ ለሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 50,000 /አምሳ ሽህ ብር/፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ብር 4,000 /አራት ሽህ ብር/፣ሎት 4 የመኪና ዘይትና ቅባት ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ ለሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም፡፡ ስለሆነም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
  13. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ እና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የተሳሳተ (ሥርዝ ድልዝ) የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስቀጣል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 79 04 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
  • ከየሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  • ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች የተቀመጡትን ናሙናዎች በማየት ዋጋ ሊሞሉ ይገባል፡፡

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here