ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
88

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኘው ለጃናሞራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በUNDP በጀት ለቅድመ 1ኛ ክፍል ህፃናት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የህፃናት የፕላስቲክ መቀመጫ ወንበር እና የህፃናት የፕላስቲክ ጠረጴዛ እንዲሁም ሎት 2. የተማሪዎች መማሪያ አገልግሎት የሚውል ጥቁር ሰሌዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ  ህጋዊ የንግድ ፈቃድ  ኮፒ ማያያዝ  አለባቸው፡፡
  2. የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ለተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ  ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1.5 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ  ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ከህዳር 08/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 22/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከህዳር 08/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 22/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ህዳር 23/2018 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ 9፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  11. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (በሎት) ምድብ ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ  ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  13. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን  ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ እና በተቀመጠው ሳምፕል ሲሆን ነው፡፡
  16. ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራንስፖርት እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
  17. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here