ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

የደብረታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ መገልገያ እና ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 3 የቴክስታይል ጋርመንት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ሎት 5 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 6 የግብርና ዕቃዎች እና ሎት 7 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 15 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ 1 በመቁረጥ ደረሰኙን  ኮፒ አድርገው በጨረታ ፖስታው ውስጥ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በሁለት ቅጂዎች ማለትም ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በደ/ታ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 በ16 ተኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ 3፡10 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እና የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ እና በላይ ሽያጭ ከተፈጸመ5 በመቶ (ቫት) ይቀንሳል፡፡
  11. የግዥ መጠን ብር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት (በቫት) ከሆነ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰውን መለያ (ስፔስፊኬሽን) መቀየር ወይም ስያሜ መስጠት ወይም የማስተካከል ስራ ከተሰራ እና ሥርዝ ድልዝ ካደረጉት ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  14. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ከግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ በተጠየቀው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  15. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ይሆናል፡፡
  16. አሸናፊው ድርጅት በአሸነፈበት የዋጋ ድምር 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ኮሌጁ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  18. ስለጨረታው ማብራሪያ መጠየቅ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 04 47 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ደ/ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here