ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
102

በአዊ አስተዳደር ዞን የሚገኘው የአድማስ ሁለ/የገበ/የኀ/ሥ/ ማኀበራት ዩኒየን ኃ.የተ የድርጅቱን የውስጥ አሰራር በዘመናዊ አሰራር ለማዘመን የወጣ ጨረታ ሎት1. ዩኒዮኑ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ሶፍት ዌር ማበልፀግ (ERP) System (የዋና ቢሮ እና የፋብሪካ አጠቃለይ የፍይናንስ ስራ ፤ የፋብሪካ ጥሬ ዕቃ እና ያለቀለት ምርት ፤ የሰብል ግብይት ፤ የግብርና ግብአት ፤ የኢንድስተሪ ምርት ግብይት የኢንቨንተሪ ሲስተም (inventory system) የሰው ሀይል አሻራ (Biometric and finger print software development )  መስራት፣ሎት2. የፒፒ ቀረጢት እና ምንጣፍ ፋብሪካ የተለያዩ ኖርማላይዜሽን ማሰራት እና የማሽን ፐርፎርማንስ መለካት ፣ሎት3. የመኪኖች ጂፒኤስ ግዥ እና የጂፒኤስ ኢንስታሌሽን ስራዎችን ከተጫራቾች በሚቀርበው ሰነድ በቴክኒካል እና ፋይናንሻል አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ  ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት በኢትዮጵያ ብር 50 (ሃምሳ ብር)  ብቻ ከፍሎ የዩንዬኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር  የጨረታ ዝርዝር ሠነዱን በመግዛት የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) የድርጅቱን ስም፣ማኀተም እና በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቹ በዋጋ ማቅረቢያ በተዘረዘረው መሠረት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ያሳውቃሉ፡፡
  4. የጨረታ ተሳታፊዎች የመሸጫ ዋጋችሁን በሠንጠረዥ በተገለፀው ዝርዝር ሁኔታ መሠረት መሙላት የምትችሉ መሆን አለበት፡፡
  5. የጨረታ ዋጋው ከመገለጹ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረገጋጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  6. ከዚህ በፊት በዘርፉ ከሰሩበት መ/ቤት የመልካም ስራ አፈፃፀም ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ተጫራቾች በሎትም በጥቅልም መወዳዳር ይችላሉ፡፡
  8. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል፡፡
  9. የጨረታ ሠነዱን ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ወይም ከህዳር 03/2018 እስከ ህዳር 18/2018 ዓ.ም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል፡፡የጨረታው መከፈቻው የህዝብ በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም ለጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊው እንደታወቀ አሸናፊው የአሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10በመቶ ለውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ5 ቀን ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታ ማስከበሪያው ሁለት በመቶ ይወረስበታል፡፡
  11. ከጨረታው ጋር በተያያዘ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ተገዥ የሚሆኑ መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ 058 227 16 81/09 98 01 27 00 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድማስ ሁለ/የገበ/የኀ/ሥ/  ማኀበራት ዩኒየን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here