በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕከላዊ አ/ርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳዉ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለት (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከማዕ/አ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመክፈል ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነና ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 05/2018 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ታህሳስ 06/2018 ይከፈታል፡፡ ባይገኝም በወቅቱ ለሚተላለፈዉ ሁሉ ተገዥ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዥ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቅዳሜና እሁድ ወይም በአል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን እና በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

