ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
67

የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት 1 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 ፈርኒቸር፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 5 ጽዳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዛው እቃ ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከህዳር 3/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ፖስታው በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በታሸገ ፖስታ ባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 30/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ካሸነፉበት ቀን ጀምረው ውል በመውሰድ ሥራ መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች እኛ በሠጠናቸው ዋጋ አሸንፈው በሚመለከተው መሠረት የእያንዳንዱን እቃ (አገልግሎት) ብዛት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
  12. መ/ቤቱ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ዝቅተኛ ጠቅላላ ዋጋ ድምር ያቀረበዉን ነው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 21 ወይም ስልክ ቁጥር 058 226 65 11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here