በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ኮፒውተር ፕሪተር ላፕቶፕ፣ ሎት 3 ተገጣጣሚ እቃዎች ማለትም ወንበር ጠረጼዛ ሸልፍ እና ሎት 4 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በየዘርፍ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክሲ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ዘወትር በስራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉዱ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፋያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ 1ኛ የወጣውን ውል እስከሚወስድ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስም፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሥዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን ህዳር 30/2018 ዓ.ም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ለአ/ጊስ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣት በባለሙያና በጥራት ኮሚቴው ስለእቃው ጥራት በማስፈተሸ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 118 08 46 /09 35 28 46 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአምባጊዮርስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

