የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል አድራሻ ባሕር ዳር አባይ ማዶ ቀበሌ ህዳር 11 ከኮበል ኢንዱስትሪ ጎን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ሎት 1 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የብስክሌት መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት 6 የህክምና እቃዎች፣ ሎት 7 ብረታ ብረት፣ ሎት 8 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 9 ጫማዎች፣ ሎት 10 ሸሚዝ፣ ሎት 11 ስፊት፣ ሎት 12 የኬን ገመድ እና ሎት 13 ሴንቴቲክ ሌዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋዉን ጠቅላላ አንድ በመቶ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ዋጋቸዉ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር / በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ማዕከሉ ከሚገዛዉ ዕቃ የዋጋዉን 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለዉ፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ማስረከቢያ የዉሉን ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የእቃዎችን አይነት (ሞዴል) ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን 3:30 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም የሚወረስ ይሆናል፡፡
- ማዕከሉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 321 54 82 /058 820 97 84 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል

