ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
68

በማእከላዊ ጎንደር ዞን የአይከል ሆስፒታል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ አቅርቦቶችም ሎት 1 የዉሃ እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የኦክስጅን ሙሌት ግዥ ሎት 5 የኦክስጅን ጭነት የትራንስፖርት ዋጋ ግዥ፣ ሎት 6 የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ እና ሎት 7 የህንፃ ቁሳቁስ እቃዎች ግዥ ናቸዉ እስከተቻለ ድረስ ውድድሩ በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን  መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የሎት የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በጀርባው ላይ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍ ማህተም ስም ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች ሆስፒታሉ ድረስ በመምጣት ማየት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከላይ ከተጠቀሰው መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታዉን ያሸነፈዉ ተጫራች የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ የሎት ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ በጭልጋ ወረዳ ፍ/ጽ/ቤት ዉል መያዝ የሚችል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በአይከል ሆስፒታል ውስጥ ከግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአይከል ሆስፒታል አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  13. ጨረታው ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለው ጨረታው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካጋጠመ ፓራፍ /ፊርማ/ ማድረግ ይገባል፡፡ ካልተደረገ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊውን የምንለየው በሎት ድምር ወይም በነጠላ ድምር ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ ከጨረታዉ ከእያንዳንዱ ሎት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በሳምፕሉ መሰረት ባይቀርቡ በኪሳራው መ/ቤቱ የማይጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  18. አሸናፊዉ ተጫራቾች በተቀመጠላቸው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት እና ሆስፒታሉ በመረጠው የጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ በተጠየቀው መሰረት ካልቀረበ በኪሳራው ሆስፒታሉ የማይጠየቅ መሆኑን ጨምረን እንገልፃለን፡፡
  19. የጨረታዉ መክፈቻ ቀን በአል ወይም እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ  በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት ይከፈታል፡፡
  20. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የድርጅታቸዉን ክብ ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡
  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው ከቡድን መሪዉ ቢሮ ቁጥር 51 በስልክ ቁጥር 058 333 01 83 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት በአሸነፈው መሰረት እቃዎችን ሆስፒታሉ ድረስ ማቅረብ የሚችልና ውሉን በጭልጋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ መውሰድ የሚችል፡፡

የአይከል ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here