የሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በደነገገው የሊዝ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 ደንብ ቁጥር 103/4004 እና ይህን አዋጅና ደንብ ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለመኖሪያ 11 ለድርጅት 1 በድምሩ 12 ቦታዎችን በጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ11 ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታን በተመለከተ ወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  5. ማስታወቂያው ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  6. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሀሳቦች /ህጎች/ ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት  ይችላሉ፡፡
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ  የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቅያ ሰሌዳ  ወይም በስልክ ቁጥር 058 667 00 39 /09 40 82 69 67 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here