ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
71

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛ በጀት ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የውሃ እቃ፣ ሎት 3 ስሚንቶ፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 6 የዉጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 7 የሀገር ውስጥ ፈርንቸር እና ሎት 8 የእንስሳት መደሀኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ከላይ በተጠቀሱት በሥራ ዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎችን ማያያዝ እንዲሁም የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የሚገዙት እቃዎች የእቃውን ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ብር ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ለእያንዳንዳቸው ሎት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 03 በመክፈል ከዋና ገ/ያዥ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 2 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 3 ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት 4 ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/፣ ሎት 5 ብር 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/፣ ሎት 6 ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ ሎት 7 ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ እንዲሁም ሎት 8 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኢትዮጵያ ብር በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጥቅል (ሎት) ስለሆነ ከተጠቀሱት እቃዎች ውስጥ አንዱንም ያልሞላ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተኛው ቀን 11፡30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በደ/ጥላ/ማ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በሥራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1 እስከ ሎት 8 በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሎት 1 እስከ ሎት 8 በደ/ጥ/ግን/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጠቅላላ እቃዎች ከደባይ ጥላት ግን ወ/ረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሥር ባሉ ንብረት ክፍሎች ድረስ በመምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ (በሲፒኦ) ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ለመንገዱ የሚያስፈልጉ  ማቴሪያል ወይም ቁሳቁስ ትራንስፖርት በተመለከተ ቦታው ድረስ ራሱ የሚያጓጉዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  1. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here