ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
49

በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ ደብረሮሀ ቅርንጫፍ ነ/ፈጅ ሶፎኒያስ ጎሹ እና በአፈ/ተከሳሽ 1. ገብረማርያም ሰጠኝ፣2 ደጀን አበበ መንገሻ፣3 ጣሰው ማረጉ ጌታው፣ 4 እንጉዳይ ይልማ ደሳለ፣ 5 ትርንጉ ደሳለ አለሙ፣ 6 ጉዳዳ ሲሳይ እማኙ፣ 7 በቀለ ቸሩ አለሙ፣ 8 አበበ ገላው ደመነ፣ 9 ጥላሁን ወሰኔ ብርሃኑ እንዲሁም 10 በላይነሽ መላክ አረቂ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ቦታው ደብረ ሲና እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ አዋሳኙም በምሥራቅ የተከዜ መነኮሳት ቦታ፣ በምዕራብ የእግር መንገድ፣ በሰሜን ሰማይነሽ ሰማው እና በደቡብ አባ ሀፍተ ጊዩርጊስ የሚያዋስነውን በወ/ሮ ጎዳዳ ሲሳይ ስም በካርታ ቁጥር ላከ/አ/በአ/1662/2002 በቀን በ25/06/2002 ዓ/ም ተመዝግቦ የሚገኘው የጭቃ ኤል ሸኘ ቤት የግምቱን መነሻ ዋጋ ሳይጠብቅ ከፍተኛ ዋጋ ለሚያቀርብ ተጫራች በጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ የጨረታው ማስታወቂያ ከህዳር 15/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15/2018 ዓ/ም ድረስ 30 ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ (መግዛት) የሚፈልጉ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መግዛት (መጫረት) የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን 25 በመቶ ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here