በሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር የደቡብ አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ዓመታዊ ግዥ ማለትም፡- ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ቆሚ የጽፈት መሳሪያ ሎት 3 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 4.የኮምፒውተርና የፎቶ ኮፒ ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳድር ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንንዱ ሎት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መረጃ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ ደቡብ አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስገባት ይችላለሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኃላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡ ውል የማይወስድ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ዉድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ደቡብ አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በየንብረት ክፍሉ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 09 18 80 32 45 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሰ/ ጎጃም ዞን አ/ የደቡብ አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

