ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

የፈረስ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒል ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ሱሰንቶምፕ ሰን ፋውንዴሽን የፈረስ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እድሳትና ጥገና ለማድረን ማለትም የሆስፒታሉን የዉጭና የዉስጥ ቀለም ቅብ፣ የአጥር ዙሪያና የቆሻሻ ማስወገጃ አጥር በሁለት ኮርስ ማሰራት፣ የቲቢ እና የትሪያጅ እንዲሁም የ3ቱ ክፍል ፓርቲሽን ማስፋፊያ ግንባታ፣ የወላድ ክፍል እና መሄጃ የሴራሚክ ንጣፍ ሥራ ሱስንቶምፕ ሰን በጀት ፋዉንዴሽን ድጋፍ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ፡-

  1. በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (ሰርተፊኬት) ያወጡና የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ጨረታው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሚገመቱ የጨረታ ሰነዶች (የቫት) ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች ከደረጃ 9 እና በላይ መሆናቸዉን ማስረጃ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትና ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋዉ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  7. ጨረታው ከህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና ጨረታዉ በዚሁ ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን ማለትም ህዳር 30/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ እለቱ ህዝባዊ በዓል ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ጠዋት 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  9. ዝርዝር ሰነዱን ከፈረስ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. አሸናፊ የሆነዉ ድረጅት አሽናፊነቱ ከተገለጽበት ቀን በ5 የሥራ የቅሬታ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋዉ ብር 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (በሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 244 00 92 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. በጨረታዉ ለኢንተርፕራይዞች ልዩ አስተያይት አይደረግም ወይም እንደማንኛዉም ተጫራቾች ብቻ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

የፈረስ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here