ሩሲያዊው አባወራ ከባለቤቱ ጋር ገበያ ወጥቶ ተዘዋውሮ ቁሳቁስ ላለመሸመት የራሱን መኪና በመስረቅ ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት ለንባብ አብቅቶታል::
በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ጥቅምት ወር የክራስኖያርስክ ከተማ ፓሊስ ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2024 ዓመት ተፈፀመ የተባለን የመኪና መሰረቅ ሪፖርት እና ከቀናት በኋላ ተሽከርካሪዋ መገኘቷ በእለት ሁነት መመዝገበያ መስፈሩን ይመለከታል::
ፓሊስ ከተመዘገበው የወንጀል ድርጊት ሁኔታ በመነሳትም ሁነቱን መከታተል እና የማጣራት ተግባርን ይጀምራል::
በእለት ሁኔታ መመዝገቢያ መዝገብ ኦንዲት ሴት የባለቤቷ ቱዮታ ኮሮላ መኪና በቤታቸው አቀራቢያ ካለ ማቆሚያ ቦታ ተሰርቃ መጥፋቷን በስልክ ለፓሊስ አሰታውቃለች:: ከጥቂት ቀናት በኋላም ያችው ሴት ተሽከርካሪዋ በዛው ቀጣና ደሴት ላይ መገኘቷ በእለት ሁኔታ መመዝገበያ ሰፍሮ ይመለከታሉ- ፓሊሶች::
የቀጣናው ፓሊስም ሁኔታው ግራ አጋብቶት የመርማሪ ቡድን አቋቁሞ ተሽከርካሪዋ ተገኘች ወደ ተባለበት ደሴት አምርቶ አሰሳ እና የማጣራት ስራ ይጀምራል:: በማጣራት ሂደቱም ተሽከርካሪዋን በጥንቃቄ ይፈትሻሉ:: የተሽከርካሪዋ በር ተሰብሮ የሞተር ማስነሻ ገመዶች ተበጣጥሰው እንድትሽከረከር ወይም እንድትንቀሳቀስ መደረጉን ያረጋግጣሉ::
ሁኔታው ያጠራጠራቸው ፓሊሶች በመጀመሪያ የማጣራት ሂደት ተጠያቂ የአቤት ባይዋን ባለቤት ወይም አባወራ ያደርጋሉ:: ለአባወራው ላቀረቡለት ጥያቄ የሰጣቸው መልስ አላሳመናቸውም፤ እንዲያውም ጥርጣሬን ያጭርባቸዋል::
ቀጥለውም ቀላል የሚመስሉ ጥቃቅን አጠራጣሪ ሁነቶችን ማወቅ በሚያስችሉ መስቀለኛ ጥያቄዎች ያፋጥጡታል፤ አባወራው ቀስ በቀስ ወደ ደበቀው ወይም ወደ ሸሸገው እውነት ያመራል::
አባወራው ከባለቤቱ ጋር በየገበያው፣ በየሱቅ እያሽከረከረ ላለመጓዝም የራሱን መኪና ያለአግባብ በግድ ማስነሳቱን እና ራቅባለ ደሴት ወስዶ መደበቁን መረዳት ችለዋል::
በመጨረሻም በሩሲያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ 306 “ሆን ብሎ የሀሰት ውንጀላ” “ኖውይንግሊ ፎልስ ዲናውንሴሽን” ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በሁለት ዓመት እስር መቀጣቱን አስነብቧል- ድረ ገጹ::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም


