በም ሥራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች መገልገያ የሚሆን ቢሮ ግንባታ ማቴሪያል ችሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ከሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ከረዳት ገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥቅል ዋጋ ለግንባታ ግዥዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 900,000 /ዘጠኝ መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ገቢ መደረግ እና ደረሰኙ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መያያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የቢሮ ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ፐሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዘዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank grante/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ግንባታውን ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ ከመሀንዲሱ ግምት ዝቅ ብሎ ከሞላ Cost breakdown እና projeket work schedule እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ /conformation letter/ አሸናፊነት ከተገለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት የተጋነነ ዝቅተኛ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የግንባታ ተቋራጭ ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡ የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የነበረው ተሻሽሎ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል፡፡
- የግንባታ የሂሳብ ስሌት በተመለከተ (አርቴሜቲክ ቸክ) በግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ባለሙያ ከሚያስተካከለው ውጭ በተጫራቾች በሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ለግንባታ ለፋይናስ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈል ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ ከሂሳብ ስሌት (አርቴሚቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ተጫራቾቹ ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቴሜቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ብቻ ተቀባይ የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታ ሥራዎች ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ለመ/ቤቱ እና ለተጫራቾች ደህንነት እንጅ እንደ መወዳደሪያ መስፈርት አይሆንም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 ጋዜጣው በወጣ በ22 ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ስዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚቀርቡት ዋጋ ማንኛውም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ በአንድ ሎት የተቀመጡትን ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 05 /058 661 19 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ግንባታውን ሰርቶ የሚያጠናቅቅበት ጊዜ 210 ተከታታይ ቀናት (7 ወራት) ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ የሚችል፡፡
- ለግንባታው ሥራ በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለግንባታው የሚጠቀሟቸው የግንባታ ማቴሪያሎች በሙሉ በባለሙያ እየተረጋገጡ ሲያልፍ ለግንባታው ሥራው ጥቅም ላይ የሚውሉ ይሆናል፡፡
- የግንባታው የሚቀርበው አሽዋ ጥራቱን የጠበቀ የአባይ አሽዋ መሆን አለበት፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

