ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
37

የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ሰዲስ/ግጨ/001/2018

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣዉን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡  ሎት 1. ፓስታና ማካሮኒ፣ ሎት 2. የግድግዳ ሚስማር እና ቆርቆሮ፣ ሎት 3. አንደኛ ደረጃ የዳቦ ዱቄት፣ ሎት 4. የመጸዳጃ ቤት ወረቀት፣ ሎት 5. የተለያዩ መጠን ያላቸዉ የልብስ ሳሙና እንዲሁም ሎት 6. ፈሳሽ የሱፍ ዘይት ፤ በመሆኑም በጨረታዉ መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በጨረታ በተራ ቁጥር 1-5 የሚሳተፉት አምራች ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ ማለትም ፓስታና ማካሮኒ፣ የግድግዳ ሚስማር እና ቆርቆሮ፣ አንደኛ ደረጃ የዳቦ ዱቄት፣ ሶፍት እና የተለያዩ መጠን ያላቸዉ የልብስ ሳሙና ሲሆን በተራ ቁጥር 6 (ፈሳሽ የሱፍ ዘይት እና ፓልም የምግብ ዘይት) ለተጠቀሱት ምርቶች ከአምራች ድርጅቶች በተጨማሪ አስመጭና አከፋፋይ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸዉ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  3. ለጨረታ የተዘጋጀዉን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ደብረ ማርቆስ ትልቅ ሆቴል ፊት ለፊት ኢኢግልድ የሰሜን ዲስትሪክት ጽ/ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ዉጤቶች ግዥና ሽያጭ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰዉ መሰረት ለብቻዉ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸዉን (financial) እና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኢንቬሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ማቅረብ ይችላሉ፡
  6. ጨረታዉ በተመሳሳይ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 178 14 42 /058 178 44 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጀት ሰሜን ዲሰትሪክት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here