ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
22

በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ የፍርድ ቤት የጃናሞራ ወረዳፍርድ ቤት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 ጽዳት እቃዎች እና ሎት 4 ኤሌክትርኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር የጽህፈትና ሌሎች የጽህፈት መሳሪያ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ ህትመት ብር 20 /ሀያ ብር/ ጽዳት ብር 10 /አስር ብር/ ኤሌክትርኒክስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመውሰድ ጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ከግዥ ፋይ/ንብ/አሰ ቡድን መሪ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት ገዝተው መውስድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለሞሉት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታ ታሽጎ መቅርብ አለበት፡፡
  7. በደባርቅ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ህዳር 22/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 06/2018 በጋዜጣ የሚቆይ መሆኑ ታውቆ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ስዓት መጥተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ /ፋይ/ን/አሰ ቡድን መሪ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም በእለቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፍታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ስርዓቱ ይካሄዳል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፍትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  10. ተጫራቾች ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ ፖስታ ላይ የድረጅታቸውን ማህተም ማድርግ አለባቸው፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች የእቃ እርክክቡ ጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ ግዥ ፋይ/ንብ/አሰ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በማምጣት የሚያስረክቡ ሲሆን የትራንስፖርቱ ወጭ እንዲሁም ማስጫኛና ማውርጃ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ፍ/ቤት በአካል በመገኝት ወይም ቁጥር 058 294 02 26 /09 18 22 64 89 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  14. ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውድድሩን በሎት ድምር ወይም በተናጠል ለማድርግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here