የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቡድን በተያዘው ለ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የኤሌክትሪክ ሲቲ እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 4 የጽህፈት መሳሪያ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 የአውቶሞቲቭ እቃዎች፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ እቃዎች፣ ሎት 8 የልብስ ስፌት እቃዎች እና ሎት 9 የግብርና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩት የግዥ ዋጋ (ጠቅላላ ዋጋ) 2 በመቶ ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡15 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ሰነድ ባልተጠቀሱ ነገሮች በግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የምንለየው በሎት በተሞላው ጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያሸነፉትን እቃ ከዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተመሳሳይ እና ጥራት የሌለው እቃ ማቅረብ በህግ ያስቀጣል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮሌጁ ግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 04 12 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

