በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለስማዳ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ በመደበኛ በጀት፣ በካልም በጀት፣ በሪድ ፕላስ በጀት በአልማ በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የውሃ እቃ፣ ሎት 5. የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 6. የመኪና እና የሞተር ጎማ ሎት 7. የዶዘር ማሽን ኪራይ እና ሎት 8 የተዘጋጁ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች፡-
- ህጋዊ (ወቅታዊ) የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስማዳ ወረዳ ግ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ማህተማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ ሥርዝ ድልዝ በፍፁም የተከለከለ ነዉ፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ስ/ወ/ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለዋና ገንዘብ ያዥ ማስያዝና ያስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማቅረብና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 058 667 01 67 ደውሎ ወይም ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 በአካል ጠይቆ መረዳት ይችላሉ፡፡
የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

