የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የሃይሉክስ ሪቦ መኪና ኬሪቦይ እቃ እና ዓመታዊ የተለያዩ ህትመቶች ለማሣተም ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የሃይሉክስ ሪቦ መኪና ኬሪቦይ እቃ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ዓመታዊ የተለያዩ ህትመቶች ብር 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል የገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማለትም ከህዳር 22/2018 እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ16 ተኛው ቀን ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በሚገዙ የዕቃዎች (አገልግሎቶች) ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፍትህ ቢሮ

