የደቡብ ጎንደር መስተዳደር ዞን የደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር እንዲሁም ሎት 5 የግንባታ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው ከ1-4 ለተዘረዘሩት ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ደራ ወረዳ ገንዘብና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃ አቅርቦት 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን በማሸግ ከፖስታው ጀርባ ለደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን አይነት በመግለጽ ዘወትር በሥራ ሰዓት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናልና ሥርዝ ድልዝ የሌለበት ተጫራቾችን ስም ፊርማ፣ መህተም ጨረታውን ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለጽ በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት እለት በዓል ቀን ከሆነ የሚታሸግ እና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሰዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ (ተመስርቶ) መጫረት አይችልም፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎትም ሆነ በተናጠል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ጽ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን አይነት የመግዛት መብት አለው፡፡
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደራ ወረዳ አንበሳሜ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 258 01 41 /09 74 08 10 74 ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

