ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በመደበኛ ካፒታል በጀት 1ኛ በመደብ ጉብዳ ቀበሌ የህክምና መስጫ ማዕከል ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችና በህንፃ ተቋረጭ፣ 2ኛ ኮሚኒቲ ፋርማሲ ማዕከል ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች እና በህንፃ ተቋረጭ፣ 3ኛ በስምና ቀበሌ ዘባኖ ወንዝ የውሃ መስኖ አውታር ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ውሃ ሥራ ተቋራጮች (GC,Water license mandatory) በመስኖ ግንባታ ውሃ ሥራ፣ 4ኛ  በሶራስ ቀበሌ በሲና ወንዝ የውሃ መስኖ አውታር ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ውሃ ሥራ ተቋራጮች (GC,Water license mandatory) በመስኖ ግንባታ ውሃ ስራ ፣ 5ኛ የገበሬ መሰልጠኛ እና መጋዘን ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች እና በህንፃ ተቋረጭ እና 6ኛ የኤሌክተሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግንባታ ማስገንባትና ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተወዳዳሪዎች  በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ፡-

  1. በሚወዳደሩበት መስክ አግባብ ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለእያንዳንዱ 1ኛ ለመደብ ጉብዳ ቀበሌ የህክምና መስጫ ማዕከል ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/፣ 2ኛ ለኮሚኒቲ ፋርማሲ ማዕከል ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/፣ 3ኛ ለስምና ቀበሌ ዘባኖ ወንዝ የውሃ መስኖ አውታር ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ 4ኛ ለሶራስ ቀበሌ በሲና ወንዝ የውሃ መስኖ አውታር ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፣ 5ኛ ለገበሬ መሰልጠኛ እና መጋዘን ብር  50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር / እና 6ኛ ለኤሌክሮኒክስ እቃዎች ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ያለባቸው  ሲሆን እንዲሁም በጨረታው ካሸነፉ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋስትና ወይም የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10 በመቶ እና የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና 30 በመቶ ማስያዝ የሚችልና ውል ወስዶ የግንባታ ሥራውን በተቀመጠለት የሥራ ዝርዝርና ፕላን መሰረት መገንባት የሚችሉና እንዲሁም ለእቃ አቅርቦት በተቀመጠው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ውል ወስደው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ማንኛውም የግንባታ ዘርፍ ተጫራች የፋይናንሻል መጫረቻ ሰነዳቸውን ከሁሉም የፋይናንሻል ሰነድ ከእያንዳንዱ ገጽ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በአንድ ወጥ ፖስታ ብቻ በማሸግ በላዩ ላይ ፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን ዘርፍ (አይነት) በመግለጽማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ለኤሌክትሮኒከስ እቃዎች የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የድርጅታቸውን ማህተምና ስም ፊርማ ተደርጎበት በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትንየመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፍል ፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ይህ ጨረታ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለግንባታ እስከ 21 ኛው ቀን እና ለኤሌክሮኒክስ እቃዎች አስከ 15ኛው ቀን  11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ፖስታ ለግንባታ የፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ ለእቃዎች ኦሪጅናል የፋይናንሻል ብቻ በአንድ ወጥ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለኤሌክተሮኒክስ እቃዎች እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ለግንባታ እስከ 22ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን በቅድም ተከተል በ16ኛው ቀን እና በ22ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 3፡00 ላይ ታሽጎ ወዲያውኑ በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  (ባይገኙም) በጨረታ ገምጋሚ ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው የግልፀኝነት ማብራሪያ ወይም ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በቢሮ ስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here