ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
57

በደቡብ ወሎ ዞን ወገልጤና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የመኪና እስፔር ፓርት፣ ሎት 5 ፈርኒቸር እቃ እንዲሁም ሎት 6 ቋሚ እቃ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በሎት አወዳድሮ  መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳድር ይችላሉ፡፡

  1. አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለእያንዳዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ወገልጤና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት ከዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩትን መረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ (ቫትን) ጨምሮ 50,000 /አምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል በ16ኛው ቀን 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡00 ላይ ይከፈታል ዕለቱ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ጽ/ቤቱ በሚገዛው እቃ 20 በመቶ መቀንስም ሆነ መጨመር ይችላል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ግዥው በሎት በጥቅል የሚፈጽም መሆኑ ታውቆ ለእያንዳንዱ ዝርዝር ዕቃዎችን መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ ያልሞላ (የዘለለ)ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሞላውን የጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  14. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ ጫኝና አውራጅንም ጨምሮ ከቦታው ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
  15. ዕቃዎች በባለሙያ መረጋገጥ ያለባቸው እንደተረጋገጠ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሓላፊነቱን አይወስድም፡፡
  17. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 335 05 76 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here