በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር ሚትስቡሽ መኪና ባለ 2 ጋቤና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሟላት አለባችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋ (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣው በ16ተኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 34 87 97 62 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዊ ልማት ማህበር

