ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

የደቡብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ለደቡብ ጎንደር ዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 2 የመኪና ጎማ  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚያቀርቡ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  5. የሚገዙት የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 12 ከረዳት ገንዘብ ያዥ መግዛት /ማግኘት/ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደርበት ለሎት አንድ 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/  ለሎት ሁለት  60,000 /ስልሳ ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ 1 በመቁረጥ ደረሰኙን አብረው አሽገው ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ  15ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በ16ኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የህዝብ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢኖሩም ባይኖሩም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ከግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  12. አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ነው፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት የዋጋ ድምር 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
  14. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጥቶ ውል  መውሰድ አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር    058 441 07 53 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here