ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
60

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በስሩ ላሉ ግንባታዎች የጥገና ሥራ የኮርኒስ፣ የሲራሚክ፣ የጣራ እና ሌሎችም የጥገና ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በGC ከደረጃ 7 እና በላይ፣ የግንባታ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ፤ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የታደሰ የግንባታ ሥራ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ያቀረቡትን እቃዎች (ስፔስፊኬሽን) በሙሉ መሙላት አለባቸዉ፤ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ፤ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ገ/ያዥ መሂ 1 በመቁረጥ ኮፒ ማስያዝ ይኖርባቸኋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት  ሰነዱን መወስድ ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታዉን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የግንባታዉ አይነት በመፃፍ በገንዳውሃ ከተማ በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡ/መሪ  ግዥ ቢሮ ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ማለትም ከህዳር 22/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ/ም ከቀኑ 12፡00 ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ በ16ኛዉ ቀን ማለትም በታህሳስ 07/2018 ዓ.ም የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በገ/ውኃ ከተማ በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡ/መሪ  ግዥ ቢሮ   በግልጽ ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ስለጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በአካል በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡ/መሪ ቢሮ በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  14. ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ (ሲፒኦ) 10 በመቶ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሆኖ በምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ ውል የሚወስድ ይሆናል ውል ከያዘ በኋላ የሚፈለጉትን እቃዎች የትራንስፖርትና የመጓጓዣ እንዲሁም ሌሎች ወጭ በራሳቸው የሚሸፈን ሆኖ እቃው የስፔስፊኬሽን ችግር ቢኖርበት በራሳችሁ የሚሸፈን ሲሆን ውል ከያዘ በኋላ የሚፈለጉትን እቃዎች (ግንባታዎች) በሚፈለገው ጊዜ ባያቀርብ (ባይገነቡት) ያስያዙት የዉል ማስከበሪያ ዉርስ ሆኖ በህግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
  15. ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት ውል ይዞ ወደ ስራ ከገባ በኋላ በግንባታው ክትትል ወቅት ተቋሙ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ጉድለት አለበት የሚለውን ክፍል እንዳስፈለጊነቱ ተመሳሳይ ስራዎች ከአንዱ ቀንሶ ወደ አንዱ ማዛወር እና ማሰራት የሚችል ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. ከዚህ ጨረታ መመሪያ ጋር የዕቃዎች (ስፔስፊኬሽን) አባሪ ሁኖ የተያያዘ ሲሆን ከወጣዉ (ስፔስፊኬሽን) ወጭ መጨመር ወይም መቀነስ አይቻልም፡የጨረታ አሸናፊ የሚለየው  በዝቅተኛ ዋጋ  ጠቅላላ ድምር  ወይም በሎት  በሚያቀርብ ዋጋ  ይሆናል፡፡
  18. አሸናፊዉ ተጫራች ሰለ ርክክብ ሁኔታ ከመ/ቤቱ ጋር የሚዋዋል ሲሆን በዚሁ ቀን ካላሰረከቡ ለ10 ቀናት ያህል  ብቻ የሚራዘምላቸው ሲሆን ከመጨረሻ ቀን ጀምሮ ርክክብ ባልተፈጸመባቸው ቀናት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በየቀኑ አንድ በመቶ መቀጫ ይከፈላል፡፡ ሆኖም በዚህ መሰረት የሚታሰበው መቀጫ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ የሚበልጥ በሚሆንበት ጊዜ ሆስፒታሉ ውሉን የመሰረዝ መብት አለው ፡፡
  19. አሸናፊ ድርጅት በዉሉ መሰረት የሚጠይቁት 30 በመቶ ቅድመ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here