ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
67

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወገራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በአምባጊዮርጊስ ዙሪያ ቀበሌ ታቦት ማደሪያ ጎጥ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋም /FTC/ በደረጃ 7 እና በላይ እንዲሁም ለወገራ ወረዳ እንስሳት ጽ/ቤት በገደብጌ ከተማ እና በኮሴየ ቀበሌ ለአንድ ቀን ጫጩት ማሳደጊያ፣ ለወተት ላም እርባታ የሚሆን ሸድ እና ለዳልጋ ከብት እና ለበግ (ለፍየል) ማድለቢያ የሚሆን ሸድ ግንባታ በደረጃ 9  እና በላይ በመደበኛ ካፒታል በጀት በሙሉ ዋጋ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገነቡት ግንባታዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1.2 አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 22/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 12/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 21 ቀናት ይቆያል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም በ4፡15 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት  ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here