የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል የ2018 በጀት አመት የሚዉሉ በግልጽ ጨረታ በሎት አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ይኸውም፡- 1 ሎት ምድብ 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 2. ሎት ምድብ 2 የቋሚ እቃዎች፣ 3. ሎት ምድብ 3 የጽህፈት መሳሪያ፣ 4. ሎት ምድብ 4 የጽዳት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ 5. ሎት ምድብ 5 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ 6 ሎት ምድብ 6 የህትመት አገልግሎት ሲሆኑ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው፣ ተጫራቾች ለመወዳደር (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ለሚያስፈልጋቸዉ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በእርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን ወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፕሪንተር ቀለሞች ኦሪጂናል ስለመሆናቸው በሚወስደው ፕሪንተር ማስሞከር፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ መጥተው ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ቫትን ያላካተተ ዋጋ ቫት እንደተጨመረ ተደርጐ ስለሚወሰድ አልጨመርኩም ወይም ይጨመረበት የሚል ተጫራች ቢኖር ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል በማድረግ በየሎቱ ፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመ/ቤታችን የግ/ፋ/ን/አ/ ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከህዳር 22/2018 እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው ከሎት 1-6 ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም 11፡30 ታሽጎ ታህሳስ 07/2018 ከጠዋቱ በ3፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው ተከፍቶ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን (የመቀበል) ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ክላስተር ማዕከሉ ማሳወቅ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ በመ/ቤታችን ፋይናንስ ግቢ በማድረግ የደረሰኝን ፎቶ ኮፒ በፖስታዉ ዉስጥ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ኦርጅናሉን) በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 033 431 51 15 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል

