በደቡብ ወሎ ዞን የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 ደንብ ቁጥር 103/2004 መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ 1. ለሁለገብ ሆቴል አገልግሎት ለB+G+7 እና በላይ ግንባታ የሚውል 1 (አንድ) ቦታ በ2017 በጀት ዓመት የወጣ የነበር (መሃል ከተማ አካባቢ)፣ 2. ለሆቴል አገልግሎት ለG+4 እና በላይ ግንባታ የሚውል 1 (አንድ) ቦታ በ2017 በጀት ዓመት የወጣ የነበር (ሃውልቱ አካባቢ) እንዲሁም 3. ለሆቴል አገልግሎት ለG+4 እና በላይ ግንባታ የሚውል (ስታድየም አካባቢ) በመሆኑም ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በጋዜጣ ከወጣበት ህዳር 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ወገልጤና ከተማ አሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማሰገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ወገልጤና ከተማ አሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው ሳጥን ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ታህሳስ 1/2018 የሥራ ቀን 11፡00 ላይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ታህሳስ 02/2018 የሥራ ቀን በ4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወገልጤና ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው መጠን የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት ከ30 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚቀርቡትን የጨረታ ሰነዶች በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት ማሰቀመጥ አለባችው፡፡ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት ያልቀረበ ጨረታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የገዟቸውን የጨረታ ሰነዶች ሁሉንም ኦርጅናል መረጃ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከፖስታ ውጭ የሚቀርብ መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ አሸናፊውን ለመለየት የሚከተሉት የማወዳደሪያ መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ 80 በመቶ የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን 20 በመቶ የሚያዝ ይሆናል፡፡
- የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀፅ 47/49 የተቀመጠ ቢሆንም ግንባታውን ገንብቶ በአጭር ጊዜ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
- ቦታውን ማየት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልጽ መረሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ያወጡትን ወጭ የመጠየቅ መብት አይኖራቸውም፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 335 05 20 /09 20 44 19 35 /09 20 48 42 62 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

