በደቡብ ጎንደር ዞን በታ/ጋ/ወ የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት አመት በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የመኖሪያና የድርጅት ቦታዎች በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በደንብ ቁጥር 103/04 አንቀጽ 13/2 በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀፅ 17 በሚያዘው መሰረት አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ በብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ የማይመለስ ገዝታችሁ መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ፖስታው ቢሮ ቁጥር 1 ለተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ህዳር 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በ10ኛው ቀን ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት የምትችሉና በዚሁ ቀን በ11፡30 ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በ11ኛው የሥራ በቀን ታህሳስ 06/4/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የሚከፈት ሲሆን በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታው ይከፈታል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ካልተስማማበት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 268 02 06 /09 28 54 63 51 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

