ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኘው ለጃናሞራ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በአሰንጋ ቀበሌ ሽንጥላየ ጎጥ የእልዋ ወንዝ የእግረኛ ድልድይ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በተቋሙ የሚሸፈኑ ሥራዎች 1ኛ የቁፋሮና የአፈር ሙሌት ሥራ፣ 2ኛ የድንጋይና የአሽዋ አቅርቦት፣ 3ኛ ከአሰንጋ ቀበሌ ከአባወርጌ ማዕከል እስከ ሳይቱ ድረስ የክርስቲ እንጨት፣ የስሚንቶ፣ ብረት፣ የፎርም ወርክ (ጣውላ) ሌሎች አጠቃላይ ትራንስፖርት መጓጓዣ በተቋሙ የሚሸፈን ሲሆን ሌሎች አቅርቦቶችና ሥራዎች እንዲሁም የእጅ ዋጋ በተቋራጭ የሚሸፈን ሲሆን የኮንክሪት ሙሊቱ በባይብሬተር የሚሞላ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም መንገድ ሥራ ተቋራጭ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም መንገድ ሥራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የድልድዩን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና5 አንድ ነጥብ አምስት በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከህዳር 22/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ 9፡15 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  10. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ40 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  11. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  12. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 /24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here