ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለጃናሞራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ 500 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቢሮ G+1 ፎቅ ለማስገንባት የህንጻ ዲዛይን እና የሥራ ዝርዝር እንዲሁም የአፈር ጥናት የሚሰራ የአማካሪ መሃንዲስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. የመልካም ሥራ አፈጻጸም ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. የቲን ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሰራ አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/  በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ የሚቆየው ከህዳር 22/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ግ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከህዳር 22/2018 እስከ ታህሳስ 06/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃናሞራ ወረዳ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም 8፡00 ታሽጎ 8፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም ጨረታው መክፈቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  13. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  14. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  15. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ተጫራቾች የሰነዶች እና አጠቃላይ ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here