በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህንፃ እድሳት በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ በወረዳ አቃቢ ህግ ዉል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የግንባታ ብቃት ደረጃ ከ1-7 የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ሁሉንም ለእድሳቱ የሚያስፈልጉ የግንባታ እቃዎች በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው የብቃት ደረጃቸው ከደረጃ 1-7 ካሉት ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበው አሸናፊው ይለያል፡፡
- የሚሰራ የሥራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘዉትር በስራ ሰዓት በሳንጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ ወይም በጥሬዉ መሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒዉን በተለያየ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘዉትር በስራ ሰዓት ጨረታዉ ህዳር 22/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መዉሰድና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ22ተኛዉ ቀን ማለትም ታህሳስ 13/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በመ/ቤታችን ሳንጃ ሆስፒታል ስብስባ አዳራሽ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎቱ በጥቅል ዋጋ ሲሆን በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊ የመለየት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ወረዳ ዐ/ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ዉል መዉሰድ የሚችል፡፡
የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

