በሰሜን ጐጃም አስተዳደር ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት በወረዳው ላሉ 1ኛ. የትምህርት ጽ/ቤት ወተት አባይና ባችማ ቀበሌ አንድ አንድ ብሎክ የመማሪያ ክፍል፣ 2ኛ.የጤና ጽ/ቤት ስር ፣3ኛ. በጤና ጽ/ቤት ስር ላሉ ለይነሳ ለምርት አጠቃላይ ጤናታጠቅ ለስራ አጠቃላይ ጤና ኬላ ለእድገት መሰረታዊ ጤና ኬላ እና ለአዲስ ልደት መሰረታዊ ጤና ኬላ እና ለአዲስ ልደት መሰረታዊ ጤና ኬላ ግንባታዎች፣4ኛ. በመንገድና ትራንስፖርት ፅ/ቤት ከቻይና ካምፕ አማሪት እና ከመርዓዊ ቆለላ የመንገድ ጥገና ማሽነሪ ኪራይ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታዉን ማስገንባትና ማሽነሪዎችን ተከራይቶ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው፡፡
- የግንባታው ተጫራቾች ደረጃ ስምንት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡
- የግንባታ ተጫራቾች ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ሆነዉ የመልካም ስራ ፈፃጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ጥቅል ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-6 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለግንባታዉ በ21 ተከታታይ ቀናት እና ለማሽነሪ ኪራይ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ በሰ/ሜ/ወ/ ገን/ጽ/ቤት በግዥ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 38 መግዛት ይችላሉ፤ ነገር ግን 22ኛው እና 16ኛዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት በሞሉት ዋጋ ብር አንድ በመቶ በባክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ( ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ያልተመሰረት የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰ/ሜ/ወ/ገን/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ መጨረሻው የመዝጊያ ስዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስደም፡፡
- የግንባታው አሸናፊ ድርጅት የግንባታ ጠቅላላ ወጭዎችን ራሱ የሚሸፍን ሲሆን የማሽነሪ ኪራይ አሸናፊ ነዳጅና ቅባት የኦፕሬተር አበልና የሎቤድ ኪራይ አሸናፊዉ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ላይ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 38 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 330 04 32 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

